አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሰዋል

2018 የውድድር ዓመት በላይቤርያው Liberian International Shipping & Corporate Registry’ ‘Liscr’ እና በደቡብ ሱዳኑ ጃሙስ ያሳለፉት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መቻልን ፌርማቸውን አኑረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ሰበታ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም ከሀገር ውጭ የሱዳኑን አልአህሊ ሸንዲ ፣ የላይቤሪያውን ‘Liscr’ እና የደቡብ ሱዳኑን ጃሙስን ማሰልጠን የቻሉት አሠልጣኝ ውበተ አባተ በሁለት ዓመት ውል መቻልን ለማሰልጠን ከስምምነት ደርሰዋል።

