ሲዳማ ቡናዎች ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማሙ

ሲዳማ ቡናዎች ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማሙ

ከትናንት በስትያ ከጦና ንቦቹ ጋር በቃል ደረጃ የተስማማው ተጫዋቾች መዳረሻቸው ሲዳማ ቡና ሆኗል

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በሀገር ውስጥ እና በአፍሪካ መድረክ ለሚጠብቁት ጨዋታዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት የቡድኑን ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነውን መስፍን ታፈሰ፣ ያሬድ በባዬ እና ደስታ ደሙሙን ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ እንዲቆዩ ማድረጉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ከትናንት በስትያ ከወላይታ ድቻ ጋር ለመጫወት በቃል ደረጃ የተስማሙት ኤፍሬም ታምራት እና ውብሸት ክፍሌ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ከስምምነት እንደ ደረሰ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

 

የግራ መስመር ተከላካይ ኤፍሬም ታምራት ከዚህ ቀደም በዱራሜ ፣ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በአርባምንጭ ከተማ መጫወቱ ሲታወቅ በ2016 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል ሲታወቅ አሁን ለቻምፒዮኖቹ ለሁለት ዓመት ለመፈረም ተስማምቷል።

ሌላኛው ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው ተከላካይ ውብሸት ክፍሌ ሲሆን ከታዳጊ እስከ ዋናው ለወላይታ ድቻ በመጫወት ሲታወቅ ዘንድሮ ለቡድኑ በሃያ ሁለት ጨዋታዎች 1833 ደቂቃዎች ተሳትፎ በማድረግ አንድ ጎል በማስቆጠር ቡድኑ ከመውረድ ስጋት እንዲላቀቅ የራሱን አስተዋፆ ማድረጉ ሲታወስ አሁን ለሲዳማ ቡና ለሁለት ዓመት መጫወት ተስማምቷል።