የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

ሞዛምቢክ ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ስብስቧን ይፋ አደረገች

ዩጋንዳ፣ ኬንያ እና ታንዛንያ በጣምራ ለሚያዘጋጁት የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ የተደለደለችው እና በምድብ ማጣሪያው አራተኛ እና አምስተኛ ጨዋታዎች ዋልያዎቹን የምትገጥመው ሞዛምቢክ ስብስቧ ይፋ አደርጋለች።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሞዛምቢካዊው ፍራንሲስኮ ኲሪዮል ኮንዴ ጁንየር ከኢትዮጵያ ጋር ለሚያደርጓቸው ሁለት ጨዋታዎች 26 ተጫዋቾች የያዘው ስብስብ ይፋ ሲያደርጉ የመጀመሪያው ጨዋታ ከ 15 ቀናት በኋላ በዕለተ አርብ ሕዳር 5 42,000 ደጋፊዎች በሚይዘው ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ በዕለተ ማክሰኞ ሕዳር 8 በባህርዳር ስታድየም ይከናወናል።

የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከሴኔጋል ጋር አቻ ተለያይቶ በሁለተኛው ጨዋታ ሱዳንን አራት ለአንድ አሸንፎ በአራት ነጥብ ሴኔጋልን በጎል ክፍያ በልጦ ምድቡን በቀዳሚነት በመምራት እንደሚገኝ ይታወቃል።