ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ደደቢት ኮት ዲ ኦርን በመልስ ጨዋታ ያስተናግዳል

ደደቢት በካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የሲሸልሱን ኮት ዲ ኦርን በመልስ ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ደደቢት ኮት ዲ ኦርን ከሜዳው ውጪ ፕራስሊን ላይ 3ለ2 አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡ በጨዋታው ላይ ደደቢቶች በሲሸልሱ ጨዋታ ላይ የተጠቀሟቸውን ተጫዋቾች ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለሶከር አትዮጵያ የሰጡት የደደቢቱ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እንዲህ ባለ መልኩ ነበር፡፡ “በሲሸልሱ ጨዋታ ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ላይ ማንንም አልጨመርንም፡፡ ያሬድ ዝናቡ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ ከኛ ጋር ወደ ባህር ዳር አልተጓዘም፡፡ ብርሃኑ ቦጋለ እና አክሊሉ አያናው አሁንም ሙሉ ለሙሉ ከጉዳታቸው አላገገሙም፡፡” ብርሃኑ ቦጋለ እና አክሊሉ አያናው አሁንም ከቡድኑ ጋር ይገኛሉ፡፡ የቋሚ አሰላለፍ ላይ ይገባሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጫዋቾች ውስጥ መካከል ናቸው፡፡

በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ የታዩ የመከላከል ክፍተቶች ላይ ደደቢቶች ጠንካራ ስራ መስራታቸውን አሰልጣኝ ዮሃንስ ገልፀዋል፡፡ “የታዩብንን የመከላከል ድክመቶች ቀርፈን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን፡፡ የመከላከል ስህተት ላለመስራት ከተጫዋቾቹ ጋር ተነጋግረናል፡፡ ነገር ግን በእግር ኳስ ስህተት ያጋጥማል፡፡ በተቻለ መልኩ በሜዳችን አሸንፈን ለመውጣት እንሞክራለን፡፡”

ደደቢት ኮት ዲ ኦርን ዛሬ በ10 ሰዓት ላይ በባህር ዳር ብሄራዊ ስታዲየም የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *