ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ስለ ጨዋታው
“ሁለታችንም ተሸንፍን እንደመምጣታችን በዛሬው ጨዋታ በነበረው እንቅስቃሴ ተሸናንፎ ለመውጣት ከፍተኛ ፉክክር ነው ያደረግነው፡፡ በ09:00 ጠራራ ፀሀይ ነው የተጫወትነው፡፡ ያም ቢሆን በሁለታችን በኩል በጎል የታጀበ መልካም እንቅስቃሴ አድርገናል፡፡ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በትኩረት ማጣት የተነሳ አቻ ወጣን እንጂ ማሸነፍ ይገባን ነበር፡፡”
የማጥቃት አማራጭ አለመኖር
” የምንፈልገውን ታክቲክ መተግበር አልቻልንም፡፡ በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ያሰብነውን ማሳካት አልቻልንም፡፡ ያ ደግሞ የስኳድ ጥበትና የአጥቂ አማራጫችን መሳሳት ነው፡፡ ፒተርን ብቻ ነው ቀይረን ያስገባናቸው ቢሆኑም ገና ለሊጉ አዲስ የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው ፤ ልምዱ የላቸውም፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ተጨምሮ ተከላክለን በመልሶ ማጥቃት ውጤት ለማስጠበቅ የነበረን ሀሳብ አልተሳካም፡፡ ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁ የሚያስከፋ አይደልም፡፡ ”
መሳይ ተፈሪ – ወላይታ ድቻ
” ጨዋታው ጥሩ ነበር፡፡ ሁለታችንም ፈጥነን ነበር ጎሎች ያስቆጠርነው፡፡ በቡድኔ በኩል ሁለት ጨዋታ ላይ ውጤት አጥተን ስለነበር የተጨዋቾች እና የአጨዋወት ለውጥ አድርገን ለማሸነፍ ጥረት አድርገን ነበር ። የመጀመርያው አጋማሽ ጎል ከማስተናገዳችን በፊት ጥሩ የጎል አጋጣሚዎችን ፈጥረን ነበር ፤ አልተሳካልንም፡፡ ያም ቢሆን ጥረታችን ተሳክቶልን ከመሸነፍ አንድ ነጥብ ይዘን ወተናል”
አዳዲስ ተጨዋቾች ስለመጠቀም
” እንደምታዩት ለሊጉ አዲስ የሆኑ በቋሚነት የመሰለፍ እድል ያገኙ ተስፋ ሰጪ የሆኑ ተጨዋቾችን ተመልክተናል፡፡ ጥሩም ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ልምድ እያገኙ ሲሄዱ የተሻለ ነገር ያሳያሉ ብዬ አስባለው፡፡ በዛሬው እንቅስቃሴያቸው ደስተኛ ነኝ፡፡
የመከላከልና ጎል የማስቆጠር ድክመት
” ያው ከምንም ሁለት ይሻላል ፤ ወደ ፊት እያስተካከልን እንሄዳለን፡፡ ያም ቢሆን ወላይታ ድቻ አቻ የሚወጣ ጎል የማይቆጠርበት ቡድን ይባል ነበር፡፡ አሁን ያንን እየተውን የሚገባበት የሚያገባ እየሆነ ነው ያለው፡፡ የሚገባብንን እየቀነስን ወደ ድሮ ጠንካራ መከላከላችን እየመጣን ጎል የማስቆጠር ችግራችንን እየቀረፍን እንመጣለን፡፡”