ሀዋሳ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሀይቆቹ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

በአሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው እየሰሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር እንዳጠናቀቁ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው ወደ አሳዳጊ ክለቡ የተመለሰው ተጫዋች ተስፉ ኤልያስ ነው፡፡ የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው ይህ ተጫዋች ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ ለዋናው ቡድንም ጭምር ከዚህ ቀደም ግልጋሎት መስጠት የቻለ ሲሆን በመቀጠል ወደ ወላይታ ድቻ እንዲሁም ደግሞ ያለፈትን አራት ዓመታት ደግሞ በሲዳማ ቡና ቆይታን ካደረገ በኋላ ዳግም ሀዋሳን ተቀላቅሏል፡፡

ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ብሩክ ኤልያስ በይፋ ለሀዋሳ የፈረመ ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ የክለብ ህይወቱን በደቡብ ፖሊስ የጀመረው የ2010 የከፍተኛ ሊግ ኮከብ ተጫዋቹ ብሩክ ከአምስት ዓመታት የደቡብ ፖሊስ ቆይታው በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ ሀምበሪቾ ዱራሜ ሲጫወት የነበረ ሲሆን አሁን ዳግም ወደ ትውልድ ከተማው የመለሰውን ዝውውር አገባዷል።