ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢብራሂማ ፎፋናን በይፋ አስፈረመ

የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ቀደም ለመፈረም ከክለቡ ጋር ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢብራሂማ ፎፋናን ዛሬ በይፊ አስፈርሟል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ በመፈረም ወደ ኢትዮጵያ የመጣው አይቮሪኮስታዊው የቀድሞ የሴዌ ስፖርት እና ስታደ ቱኒዚየን የመስመር አጥቂ በኤሌክትሪክ የአንድ አመት ቆይታው በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አስደናቂ አቋሙን መሳቱን ተከትሎ በሊጉ የተጠበቀበትን ያህል ባይሆንም መልካም የውድድር አመት አሳልፏል፡፡

ፎፋና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለት አመታት ኮንትራት የፈረመ ሲሆን በዝውውር መስኮቱ ምርጥ የሚባል ዝውውሮች እያከናወነ የሚገኘውና 7 ተጫዋቾችን ያስፈረመው ቅዱስ ጊዮርጊስን የአጥቂ መስመር ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *