​ድሬዳዋ ከተማ ጋናዊው ጌዲዮን አካክፖን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ላለመውረድ ሲጫወት የነበረው ድሬዳዋ ከተማ በዘንድሮው ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እያመጣ ይገኛል፡፡ አሁን ደግሞ ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ጌዲዮን አካክፖን አስፈርሟል፡፡
በ2004 ድሬዳዋ ከተማን በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ጌድዮን በሙገር ሲሚንቶ እና ሀዋሳ ከተማ እስከ 2007 የውድድር አመት መጫወት ችሎ ነበር፡፡ ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በሚያንማር ያንጎን ዩናይትድ ክለብ አሳልፎ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለድሬዳዋ ከተማ የአንድ አመት ውል ፈርሟል፡፡

ጌዲዮን በደቡብ ካስትል ዋንጫ ላይ ዛሬ ክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተሰልፎ  መጫወት ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *