​የፕሪምየር ሊጉ የ2010 ድልድል ይፋ ሲሆን የሚጀመርበት ጊዜም በድጋሚ ተራዝሟል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2010 ውድድር አመት የእጣ ማውጣት ስነስርአት በዛሬው እለት በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል፡፡ 

በወጣው እጣ መሰረት የመጀመርያው ሳምንት መርሀ ግብር ይህንን ይመስላል፡-

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ

ኢትዮጵያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና

አርባምንጭ ከተማ ከመቐለ ከተማ

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ከ ፋሲል ከተማ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ

ጅማ አባ ጅፋር ከ ሀዋሳ ከተማ

ወልድያ ከተማ ከአዳማ ከተማ

ደደቢት ከ ወላይታ ድቻ

በስነስርአቱ ላይ እንደተገለጸው ሊጉ የሚጀመርበት ጊዜ በውል ያልታወቀ ሲሆን እንደ አየር ሁኔታ ለውጡ እደታየ እንደሚወሰን ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊጉ ጥቅምት 4 እንደሚጀመር ማስታወቁ የሚታወስ ቢሆንም የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ለማከናወን ጊዜው እንዲገፋለት በመጠየቁ እና በሌሎች ምክንያቶች ወደ ጥቅምት 11 መራዘሙ ይታወሳል። ለሁለተኛ ጊዜ በሜዳዎች አለመመቸት እና በዝናብ ምክንያት ፌደሬሽኑ ከጥቅምት 11 ወደ ጥቅምት 20 ማዘዋወሩን ዛሬ የገለፀ ሲሆን አሁንም ግን ሊፈጠሩ በሚችሉ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ሜዳዎች ለጨዋታ ብቁ መሆን አለመሆናቸው ተፈትሾ ወደ ጥቅምት 27 ሊገፋ እንደሚችል ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *