ወልዋሎ በሙሉዓለም ጥላሁን ላይ የዲሲፕሊን ቅጣት አስተላለፈ

ያለፈውን አንድ ወር ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ርቆ የቆየው ሙሉዓለም ጥላሁን በክለቡ የዲሲፕሊን ቅጣት ማስተላለፉን ገልጿል።

ተጫዋቹ ሚያዝያ 8 ከኢትዮጵያ ቡና ካደረጉት ጨዋታ በኋላ ወደ ቡድኑ ያልተመለሰ ሲሆን ክለቡ ለሦስት ጊዜያት ወደ ቡድኑ እንዲመለስ ቢያሳውቅም መመለስ ባለመቻሉ የ2 ዓመት እገዳ እና የ580 ሺህ ብር ቅጣት አስተላልፎበታል።

የውሳኔ ደብዳቤው ይህንን ይመስላል