ወልዋሎ ከመከላከያ ጋር የተደረገው ጨዋታ የነበሩ የጨዋታ አመራሮች ላይ ክስ መስርቷል

ሚያዝያ 22 በመከላከያ እና ወልዋሎ ጨዋታ በእለቱ ዳኛ እያሱ ፈንቴ ላይ በተፈፀመው ድብደባ ዙርያ የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በክለቡ፣ በ7 ተጫዋቾች እና በቡድን መሪው ላይ ቅጣት ማሳለፉና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውሳኔውን በከፊል በመሻር የ5 ተጫዋቾች ቅጣት እንዲነሳ መወሰኑ ይታወሳል።

ክለቡ በዲሲፕሊን ኮሚቴው ቅጣት ዙርያ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ቅጣቱ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን ተከትሎ በጨዋታው አመራሮች ላይ የቀረበው ሪፖርት ላይ ጥያቄ አንስቶ ክስ መስርቷል።
ሙሉ ደብዳቤው ይህንን ይመስላል:-