ሎዛ አበራ እና ቱቱ በላይ ለሙከራ ወደ ስዊድን አምርተዋል

የደደቢቷ አጥቂ ሎዛ አበራ እና የቅዱስ ጊዮርጊሷ አማካይ ቱቱ በላይ በስዊድን ክለቦች የሙከራ ጊዜ ለማሳለፍ ዛሬ ምሽቱን ወደ ስዊድን አቅንተዋል፡፡

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ቢራ እና አአ ከተማ ያሳለፈችውና በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ጊዮርጊስ እየተጫወተች የምትገኘው ቱቱ በላይ እና የደደቢቷ ግብ አዳኝ ሎዛ አበራ ከሶስት ወራት በፊት ስዊድናዊ መልማይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከተመለከታቸው በኋላ የሙከራ እድሉን እንዳመቻቸላቸው የተገለፀ ሲሆን ፒትያ እና ሮሰንጋርድ የሙከራ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ክለቦች ናቸው ተብሏል።

ሎዛ አበራ በቅርቡ ወደ ቱርክ አምርታ በአንታናይስፖር የሙከራ ጊዜ አሳልፋ መመለሷ የሚታወስ ሲሆን የቀድሞዋ የንግድ ባንክ ግብ ጠባቂ ዳግማዊት መኮንን በቱርክ ፊርማዋን ማኖሯ ይታወሳል።