ወልዋሎ የተጫዋቾቹን ውል አድሷል

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ውላቸውን ያጠናቀቁ 4 ተጫዋቾችን ውል አድሷል። 

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ኤሌክትሪክን ለቆ ወደ ክለቡ በማምራት ቡድኑን በአምበልነት የመራው በረከት ተሰማ ለተጨማሪ ዓመት ውሉን ሲያድስ በተመሳሳይ ክለቡን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ተቀላቅለው የነበሩት ዋለልኝ ገብሬ እና ተስፋዬ ዲባባ እንዲሁም ከግማሽ ዓመት ጀምሮ ቡድኑን እያገለገለ የሚገኘው ግብ ጠባቂው ዮሀንስ ሽኩር ሌሎች ውላቸው በአንድ ዓመት የታደሰላቸው ተጫዋቾች ናቸው።

በተያያዘ በግማሽ የውድድር ዓመት ክለቡን የተረከቡት አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያም ቆይታ በቅርቡ እንደሚረጋገጥ ይጠበቃል።