ካሜሩን 2019| የኢትዮጵያ እና ሴራሊዮንን ጨዋታ የሚዳኙት ዳኞች ታውቀዋል

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ሁለተኛ የምድብ የማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሴራሊዮንን ጳጉሜ 4 ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም ያስተናግዳል። ይህን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞችም ይፋ ተደርገዋል። 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው ጨዋታውን ቱኒዚያዊው ሳዶክ ሴሌሚ በዋና ዳኝነት ሲመሩ ሊቢያዊው አቲያ አምሳድ እና ቱኒዚያዊው አይመን ኢስማይል ረዳት ዳኞች ናቸው። ቱኒዚያዊው ነስረላህ ጃኦዋዲ 4ኛ ዳኛ ሲሆን ሱዳናዊው በሻራ ናስር በኮሚሽነርነት ተመድበዋል።