ሽመልስ በቀለ ለፔትሮጄት ፈረመ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አማካይ ሽመልስ በቀለ ከግብፁ ፔትሮጄት ጋር ከስምምነት ደርሷል፡፡

የቀድሞው የሃዋሳ ከነማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አል-ኢትሃድ እና አል ሂላል ኮከብ ከሱዳኑ ክለብ ጋር ከተለያየ በኋላ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ግብፅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቶ ለፔትሮጄት ፈርሟል፡፡ የዝውውሩን ሂደት ለማጠናቀቅ አዲስ አበባ የተገኘው የተጫዋቹ ወኪል የሆነው አብዱራህማን ሜግዲም ዝውወሩ በይፋ መጠናቀቁን በትዊተር አካውንቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ሽመልስ የተዛወረበት ፔትሮጄት ከታላላቆቹ የግብፅ ክለቦች ቀጥሎ የሚጠቀስ ክለብ ሲሆን ዘንድሮ (2015) በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ ይሳተፋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *