የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 1-0 ሀዋሳ ከተማ

ከ11ኛ ሳምንት የሊጉ የዛሬ ጨዋታዎች መካከል አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ተገናኝተው ቡና 1-0 አሸንፏል። የቡድኖቹ አሰልጣኞችም በጨዋታው ዙሪያ ተከታዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል።

“ተጫዋቾቼ ያላቸውን ሁሉ ለቡና በመስጠታቸው ኮርቼባቸዋለው።” ዲዲዬ ጎሜስ – ኢትዮጵያ ቡና

” አንደኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን። ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር  ፤ ብዙም ተፋልመናል። ተጫዋቾቼም ቆራጥነታቸውን በማሳየታቸው በጣም ደስ ብሎኛል። ሦስት እና አራት ግቦችን ከማስቆጠር በላይ ዋናው ነገር መሪነታችንን ማስቀጠላችን ላይ ነው። ዛሬ በጣም ምርጡ የተከላካይ ክፍል እንዳለን አይተናል። ብዙ ተጫዋቾች የተጎዱብን በመሆኑም ከያዝነው የጨዋታ አካሄድ ጋር መላመድ ኖሮብናል። ተጫዋቾቼ ያላቸውን ሁሉ ለቡና በመስጠታቸው ኮርቼባቸዋለው። ” 

” የማጥቃት ሂደታችን ጥሩ ነው ብዬ አላስብም። ምክንያቱም የፈጠርናቸው ዕድሎች አልነበሩም። ” አዲሴ ካሳ – ሀዋሳ ከተማ

” መጀመሪያ ላይ በመዘናጋት ክፍተት ከመስጠታችን ውጪ ጨዋታው ጥሩ ነበር። በመቐለው ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍ ላይ ነበር ትኩረታችን ፤ ብዙ ዕድልም ፈጥረን በመልሶ ማጥቃት ተቆጥሮብናል። ዛሬ ግን በቶሎ ነበር የገባብን። ሆኖም የማጥቃት መንፈሱ ቢኖረንም ደፍረን መግባት ግን አልቻልንም። ኳስ እንይዛለን እንጂ ከመጨረሻው ኳስ ውጪ ያሚያጓጓ ሙከራ አልነበረንም። ምንአልባት የቡና መከላከል ሊሆን ይችላል ወደ ፊት እንድንሄድ ያደረገን ፤ ሙሉ ለሙሉ እነሱ ሜዳ ላይ ነበርን። የማጥቃት ሂደታችን ጥሩ ነው ብዬ ግን አላስብም ምክንያቱም የፈጠርናቸው ዕድሎች አልነበሩም። “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *