የአሰልጣኞች አስተያየት | “ውጤቱ ያንሰናል እንጂ አይበዛብንም” ገብረመድኅን ኃይሌ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 ካሸነፈ በኋላ የመቐለው አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ አስተያየት ሲሰጡ የኢትዮጵያ ቡናው ዲዲዬ ጎሜስን አስተያየት ማካተት አልቻልንም።

ገብረመድኅን ኃይሌ – መቐለ 70 እንደርታ

” ጨዋታውን እንደተመለከታችሁት ነው። ምንም ቅንኳ ቀሪ ጨዋታዎች ቢኖሩንም በብዙ የነጥብ ልዩነት መርተውን ስለነበር የግድ ይህን ወሳኝ ጨዋታ በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ የመጠጋት ግዴታ ውስጥ ሆነን ነበር የገባነው። ሌላው እነሱ ከኛ የተሻለ ነጥብ ሰብስበው ወደዚህ ጨዋታ ስለገቡ በተሻለ ተነሳሽነት እና ነጥብ ይዘው ለመመለስ አስበው ነው የተጫወቱት። ነገር ግን እንደተመለከታችሁት ይህ ውጤት ለኛ ያንሰናል እንጂ አይበዛብንም።

” የዛሬው ውጤት ከማሸነፍ በላይም ነበር። በአጠቃላይ ተጫዋቾቼ ያሳዩት እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ። “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *