ደደቢት የቀድሞ ተጫዋቹን አስፈረመ

ባለፈው ሳምንት ከስሑል ሽረ በስምምነት የተለያየው አሸናፊ እንዳለ ወደ ቀድሞ ክለቡ በድጋሚ ተቀላቀለ።

ባሰናበቷቸው በርካታ ተጫዋቾች ምትክ በሰፊው ወደ ገበያው የወጡት ደደቢቶች ባሳለፍነው ሳምንት አንድ ዓመት ተኩል ከቆየበት ስሑል ሽረ በስምምነት የተለያየው ግዙፉ አማካይ አሸናፊ እንዳለን አስፈርመዋል። በደደቢት፣ በቡራዩ ከተማ፣ አውስኮድ እና ስሑል ሽረ መጫወት የቻለው አሸናፊ እንዳለ ደደቢቶች በዚህ የዝውውር መስኮት ያስፈረሙት አራተኛ ተጫዋች ሆኗል።

ባለፈው ወር አጋማሽ አሰልጣኞቹን በማሰናበት ዳንኤል ፀሐዬን ቀጥሮ በርካታ ተጫዋቾች ያሰናበተው ደደቢት በቀጣይ ቀናት ባሰናበታቸው ምትክ በርካታ ተጫዋቾች ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *