” በእርግጠኝነት እናሸንፋለን ብለን ነው የመጣነው” – ዘርዓይ ሙሉ – ሲዳማ ቡና

ሲዳማ ቡና ዛሬ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ከረታበት ጨዋታ በኋላ የቡድን ዋና አሰልጣኝ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማ ከመልበሻ ክፍል ሳይወጡ ረጅም ጊዜ በመቆየታቻው አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም።

ውጤቱን ስለመጠበቁ እና ስለጨዋታው

“ውጣቱን ጠብቄዋለው ማለት ይቻላል። ለማሸነፍ ነው የመጣነው። ወደ ዋንጫው እየተጓዝን ስለሆነ የነበረን አማራጭ አንድ እና አንድ ማሸነፍ ብቻ ነው። ስንጀምር አስር ደቂቃ ጥሩ ነበርን። ከዛ በኋላ ግን አንድ ሃያ ደቂቃ ተበላሽቶብን ነበር። እረፍት ልንወጣ አካባቢ ደግሞ ወደ ሪትሙ ተመልሰናል። ከዕረፍት በኋላ ግን የተጫዋቾች ቅያሪ አድርገን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር አሸንፈን ወጥተናል። በእርግጠኝነት እናሸንፋለን ብለን ነው የመጣነው ፤ ተዘጋጅተንም ነበር።”

በዋንጫው ፉክክር ውስጥ እንዳሉ ስለማሰቡ

“በፉክክሩ ውስጥ መኖራችን ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ጠንካራ ጨዋታዎቻችንን በመጨረሳችን የተሻለ ዕድል ያለን እኛ ነን። ስለዚህ እንደዚህ ጥንቃቄ አድርገን የምንጫወት ከሆነ ቀሪዎቹን ጨዋታዎችም አሸንፈን ቻምፒዮን እንሆናለን ብዬ አስባለው።”


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡