ኢትዮጵያ ዋንጫ | ወሳኙ ጨዋታ የት እንደሚደረግ ተወሰነ

የመቐለ 70 እንደርታ እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ቀጣይ ሐሙስ በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲካሄድ ተወሰነ።

በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ እስካሁን ድረስ ያልተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜው መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ማገናኘቱን ተከትሎ ጨዋታውን የሚካሄድበት ስቴድየም የት ይሆናል በሚል የብዙዎች ትኩረት ስቦ መቆየቱ ይታወሳል። አወዳዳሪው አካል አመሻሹን ከሁለቱም ክለቦች ጋር በመምከር ጨዋታው ቀጣይ ሐሙስ አራት ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑ ሲታወቅ መቐለ 70 እንደርታ ወክለው በቦታው የተገኙት ተወካዮች ውሳኔው ከሌሎች የክለባቸው አመራሮች መክረው ውሳኔያቸው እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል።.


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡