የአለልኝ አዘነ ማረፊያ ሀዋሳ ከተማ ሆኗል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ለሀዋሳ ፊርማውን አኑሯል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ከአርባምንጭ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በቡድኑ በግሉ የተሳኩ ዓመታትን አሳልፎ ከሳምንት በፊት ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት የተስማማ ቢሆንም በጥቅማጥቅም ባለመስማማቱ ምክንያት ክለቡን ለቆ ሀይቆቹን ተቀላቅሏዋል። ከሄኖክ አየለ በመቀጠል ሀዋሳን የተቀላቀለ ሁለተኛው ተጫዋች መሆንም ችሏል።

የሶሆሆ ሜንሳህ፣ ላውረንስ ላርቴ እና ያኦ ኦሊቨርን ውል ያራዘመው ሀዋሳ በቀጣይ ቀናትም የነባር ተጫዋቾችን ውል እንደሚያራዝም እና ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን እንደሚቀላቅል አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡