የአማኑኤል ገብረሚካኤል ማረፍያ በቅርቡ ይታወቃል

በዚህ የዝውውር መስኮት በጉጉት ከሚጠበቁት ዝውውሮች መካከል የመቐለ 70 እንደርታው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል የዝውውር ጉዳይ በቅድሚያ ይጠቀሳል።

የግብፁ ኤንፒፒአይ እና ከስዊዘርላንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ክለብ በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢያሳዩም ተጫዋቹ ግን የቡድን አጋሩ ሐይደር ሸረፋን ተከትሎ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት የሚያቀናበት ዕድል የሰፋ ይመስላል።

በተለይም ከግብፁ ክለብ ኤንፒፒአይ ጠንከር ያለ የዝውውር ጥያቄ የቀረበለት ተጫዋቹ ባለፉት ቀናት ከፈረሰኞቹ ጋር ንግግር ማድረጉ ሲታወቅ የተጫዋቹ ማረፍያም ከሁለቱ ክለቦች ይልቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሆኑ ዕድል የሰፋ ነው።

ከዳሽን ቢራ ሁለተኛ ቡድን አድጎ ለሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እና ለመቐለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ በመቐለ ውሉን የሚያራዝምበት ዕድል የጠበበ መሆኑ ሲታወቅ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ማረፍያው ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ