ሪችሞንድ አዶንጎ ብርቱካናማዎቹን ተቀላቀለ

ድሬዳዋ ከተማዎች ላለፈው አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከወልዋሎ ጋር ቆይታ ያደረገው ጋናዊው ሪችሞንድ አዶንጎን አስፈርመዋል።

ገና በለጋ ዕድሜው ወደ ስዊድኑ ጉተንበርግ አምርቶ የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኃላ በ2010 ወደ ሃገሩ ጋና በመመለስ ከበርኩም ቸልሲ ፣ አሚዱስ እና ሌበሪቲ ፕሮፌሽናልስ ሶስት የተሳኩ ዓመታት ያሳለፈው አጥቂው በዛምቢያው ብዩልድ ኮን የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኃላ ነው በ2010 አጋማሽ ወልዋሎን የተቀላቀለው። በክለቡ የ18 ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላም ወደ ምስራቁ ክለብ ተጉዟል።

ወደ ዝውውር መስኮቱ ዘግይተው የገቡት ድሬዳዋ ከተማዎች ቀደም ብለው የአሰልጣኝ ስምዖን አባይ ውል በማራዘም ተጫዋቾች እያስፈረሙ ሲገኙ ቡድኑን ተቀላቅለው ከነበሩት መካከል ከዘካርያስ ቱጂ እና ፋሲል አስማማው ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ