ምንተስኖት አሎ እና መከላከያ ሊለያዩ ነው

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ፊርማውን ለመከላከያ ያኖረው ምንተስኖት አሎ ከክለቡ ጋር በስምምነት ለመለያየት ከጫፍ እንደደረሰ ታውቋል።

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ምንተስኖት አሎ ከወራት በፊት ፊርማውን ለመከላከያ በማኖር ለሁለት ዓመት በክለቡ ለመጫወት መስማማቱ ይታወሳል። ይሁንና ተጨዋቹ ዛሬ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ከሆነ ክለቡ በ2012 በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደማይሳተፍ ከታወቀ ክለቡን እንደሚለቅ እና ውሉ በስምምነት እንደሚፈርስ በውሉ በመገለፁ ጥሩን ለመልቀቅ እንደተቃረበ አስታውቋል።

ከባህር ዳር ከተማ ውጪ በሰበታ ከተማ እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለው ተጨዋቹ በኦሊምፒክ እና ዋናው ብሄራዊ ቡድን በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጥሪ ቀርቦለት መጫወቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ