ስሑል ሽረ የሦስት ነባሮችን ውል አድሷል

በትናንትናው ዕለት ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም የተስማሙት ስሑል ሽረዎች የሦስት ተጫዋቾች ውል አድሰዋል።

ሸዊት ዮሐንስ ውል ካራዘሙት መካከል ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ምሩቅ የሆነው የግራ መስመር ተከላካዩ ሽረ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያልፍ የቡድኑ ወሳኝ አባል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁንም ለቀጣይ ሁለት ዓመታትም በስሑል ሽረ ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።ሁለተኛው ከስሑል ሽረ ጋር ውሉን ያራዘመው የመስመር አማካዩ ክፍሎም ገብረህይወት ነው።
ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለተኛ ዲግሪውን የያዘው ፈጣኑ አማካይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከቡድኑ ጋር ቆይታ ያደረገ ሲሆን በተወሰኑ ጨዋታዎችም ከተቀያሪ ወንበር እየተነሳ ቡድኑን ማገልገሉ ይታወሳል።

ሦስተኛው ከቡድኑ ጋር ውሉን ያራዘመው አጥቂው ሰዒድ ሐሰን ነው። በስሑል ሽረ ከብሄራዊ ሊግ ጀምሮ በመጫወት ላይ የሚገኘው አጥቂው በተለይም ቡድኑ ወደ ከፍተኛ ሊግና ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ወሳኝ ተጫዋች የነበረ ሲሆን ባለፈው የውድድር ዓመትም በአመዛኙ ከተጠባባቂ ወንበር እየተነሳ ቡድኑን አገልግሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ