የወልቂጤ ከተማ የቀድሞ ተጫዋቾች ለፌዴሬሽኑ ቅሬታን አሰምተዋል

በወልቂጤ ከተማ በ2011 የውድድር ዘመን ሲጫወቱ የነበሩ ስድስት ተጫዋቾች ክለቡ ወርሀዊ ደመወዝ አልከፈለንም በማለት የቅሬታ ደብዳቤን ለፌዴሬሽኑ አስገብተዋል፡፡

ተጫዋቾች በደብዳቤያቸው ” ክለቡ የሁለት ወር ደመወዝ አልከፈለንም፤ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ክለቡን ብንጠይቅም ምላሽ ሊሰጥን አልቻለም። ስለሆነም ፌዴሬሽኑ ያስገባነውን ደብዳቤ ተመልክቶ ክፍያችንን ያስፈፅምልን።” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

*ተጫዋቾቹ ያስገቡት የቅሬታ ደብዳቤ👇


© ሶከር ኢትዮጵያ