ታደለ መንገሻ በመጨረሻ ሰዓት ወደ ሰበታ አቅንቷል

በዝውውር መስኮቱ ባሳለፍነው ረቡዕ ከመጠናቀቁ በፊት ታደለ መንገሻ አዲስ አዳጊዎቹ ሰበታ ከተማዎችን ተቀላቅሏል።

የእግርኳስ ህይወቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን የጀመረው ታደለ ወደ ዋናው ቡድን ማደግ ቢችልም በቂ የመሰለፍ እድል ማግኘት ባለመቻሉ በ2005 የውድድር ዘመን ደደቢትን ተቀላቅሎ እስከ 2008 የውድድር ዘመን ድረስ ስኬታማ ጊዜያትን ማሳለፍ ችሏል። ቀጥሎም በትውልድ ከተማው ክለብ አርባምንጭ ከተማ ስኬታማ ጊዜያትን በማሳለፍ በ2009 የክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚመልሰውን ዝውውር በመፈፀም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ከጉዳት ጋር እየታገለ ቆይታ ማድረግ ችሏል። በተለይም

በ2010 የውድድር ዘመን አመዛኙ የውድድር ዓመቱን በጉዳት ከስብስብ ውጭ ሆኖ አሳልፏል፤ ተጫዋቾቹ ከጉዳት ነፃ በሆነባቸው ወቅቶች እምብዛም የመሰለፍ እድል ባያገኝም የቀደመ ብቃቱን መልሶ ማግኘት እንደሚችል ተስፋ ሰጪ ነገሮችን ግን ማሳየት ችሏል። በዚህም በዝውውሩ የመጨረሻ ዕለት ጊዮርጊስን ለቆ ሰበታን ተቀላቅሏል። ሰበታዎች በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ በአንጻራዊነት የተሻለ የቴክኒክ ክህሎት ባላቸው ተጫዋቾች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ቡድን በመገንባት ላይ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ