አዞዎቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈረሙ

ቀደም ብለው ምንተስኖት አበራ እና አድማሱ ጌትነትን ያስፈረሙት አዞዎቹ አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ቀድሞ ክለባቸው መልሰዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት አርባምንጭ ከተማ ለቆ ኢትዮጵያ ቡና በመቀላቀል ከቡድኑ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት መለያየቱ ሲታወስ ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ አርባምንጭ ከተማ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወቱ ይታወሳል።

ሌላው ቡድኑን የተቀላቀለው ፍሬው ገረመው ሲሆን እሱም በተመሳሳይ ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰ ተጫዋች ነው። ከአርባምንጭ ሁለተኛ ቡድን አድጎ በዋናው ቡድንም ቆይታ የነበረው ግብጠባቂው በደቡብ ፖሊስም መጫወቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ