ለሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ወደ ታንዛኒያ የሚያመራው የሉሲዎቹ ስብስብ ታውቋል

በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እየተመራ ልምምዱን ከጀመረ አንድ ሳምንት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ዋንጫ ወደ ታንዛኒያ 20 ተጫዋቾችን በመያዝ ይጓዛል፡፡

ከጥቅምት 23 ጀምሮ ለምስራቅ መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ዝግጅቱን እያደረገ ያለው ኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኢትዮጵያ ሆቴል ማረፊያቸውን በማድረግ በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እና ረዳቶቹ እየተመራ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲዘጋጅ የቆየ ሲሆን የዝግጅት ጨዋታም ባሳለፍነው ዓርብ ማድረጉ ይታወሳል። ነገ ደግሞ ሁለተኛ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ከ15 አመት በታች የወንዶች ቡድን ጋር ይጫወታል፡፡

አሰልጣኙ አስቀድሞ ጥሪ ያቀረበላት ግብ ጠባቂ ዓባይነሽ ኤርቄሎ በቤተሰብ ሀዘን ምክንያት በጊዜ መቀላቀል ባትችልም ትላንት ወደ ስብስቡ ተካታ የፊታችን ረቡዕ ወደ ስፍራው አብራ ታመራለች። ከሀዋሳ ከተማ የተመረጠችሁ ተከላካይዋ ትዝታ ኃይለሚካኤል ከገጠማት ጉዳት አገግማ በስብስቡ መካተት ስትችል ከንግድ ባንክ የተመረጠችው ግብ ጠባቂዋ ንግስቲ መዓዛ፣ የአዳማዋ አጥቂ ምርቃት ፈለቀ እንዲሁም የመከላከያዎቹ መሰሉ አበራ እና አይዳ ዑስማን የተቀነሱ የቡድኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወደ ዳሬሰላም የሚጓዙ 20 ተጫዋቾች

ግብጠባቂዎች – አባይነሽ ኤርቄሎ፣ ታሪኳ በርገና፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ

ተከላካዮች – ትዝታ ኃይለሚካኤል፣ ገነሜ ወርቁ፣ መስከረም ካንኮ፣ ጥሩአንቺ መንገሻ፣ ዓለምነሽ ገረመው፣ እፀገነት ብዙነህ፣ ታሪኳ ዴቢሶ፣ ናርዶስ ዘውዴ

አማካዮች – ህይወት ደንጊሶ፣ እመቤት አዲሱ፣ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ፣ ሰናይት ቦጋለ፣ ገነት ኃይሉ፣ አረጋሽ ካልሳ

አጥቂዎች – ሽታዬ ሲሳይ፣ ረሂማ ዘርጋው፣ ሴናፍ ዋቁማ 


© ሶከር ኢትዮጵያ