ቅድመ ዳሰሳ | ሲዳማ ቡና ከ ስሑል ሽረ

በሃዋሳ ስታዲየም በዝግ የሚካሄደው የነገው ብቸኛ መርሃ ግብርን እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

በመጀመርያ የሊጉ መርሐግብር በወላይታ ድቻ ሽንፈት አስተናግደው ሊጉን የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች ጨዋታው ለደጋፊያቸው ዝግ ቢሆንም በነገው ጨዋታ ፈተና ይገጥማቸዋል ተብሎ አይገመትም።

የትግራይ ዋንጫ አሸናፊ የነበሩት እና በውድድሩም ስሑል ሽረን አራት ለአንድ ማሸነፍ ችለው የነበሩት ሲዳማዎች በነገው ጨዋታም ከመጀመርያው ሳምንት አቀራረብ ብዙም ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ አይገመትም።

ዘንድሮ ለኳስ ቁጥጥር ቅድምያ ሰጥተው በመጫወት የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የነገው ጨዋታ ላይ ነጥብ ጥለው መጥፎ አጀማመር ላለማድረግ በማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብተው ነው ጨዋታውን የሚያካሂዱት።

ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳዩ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳቸው በማሸነፍ ነበር ሊጉን የጀመሩት። በመጀመርያው የሊጉ መርሃግብር በመልሶ ማጥቃት በርካታ ዕድሎች ፈጥረው መጠቀም ያልቻሉት ስሑል ሽረዎች ከማጥቃቱ በተጨማሪ በመከላከል ላይ ያላቸው ክፍተቶች አርመው ወደ ሜዳ ካልገቡ በጨዋታው ላይ መቸገራቸው አይቀሬ ነው።

ስሑል ሽረዎች በግል ጉዳይ ወደ ሃዋሳ ካልተጓዘው ሃይለአብ ኃይለሥላሴ ውጪ በጉዳትም ሆነ በቅጣት የሚያጡት ተጫዋች የለም።

እርስ በእርስ ግንኙነት

– ቡድኖቹ ሁለት ጊዜ በሊጉ የተገናኙ ሲሆን ሲዳማ አንዱን ሲያሸንፍ በሌላኛው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። ሲዳማ አራት ሲያስቆጥር ሽረ ደግሞ ሦስት ማስቆጠር ችሏል።

– ለመጨረሻ ጊዜ ተገናኙት በዘንድሮው የትግራይ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ሲሆን ሲዳማ ቡና 4-1 ማሸነፉ ይታወሳል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ሲዳማ ቡና (4-2-3-1)

መሳይ አያኖ

ዮናታን ፍስሀ – ግርማ በቀለ – ጊት ጋትኮች – ክፍሌ ኪያ

ዮሴፍ ዮሐንስ – ብርሃኑ አሻሞ

ሀብታሙ ገዛኸኝ – ዳዊት ተፈራ – አዲስ ግደይ

ይገዙ ቦጋለ

ስሑል ሽረ (4-2-3-1)

ምንተስኖት አሎ

ዓብዱሰላም አማን – ክብሮም ብርሃነ – በረከት ተሰማ – ረመዳን የሱፍ

አክሊሉ ዋለልኝ – ሙሉዓለም ረጋሳ

ዲድየ ሊብሪ – ያስር ሙገርዋ – ዓብዱለጢፍ መሐመድ

ሳሊፍ ፎፋና


© ሶከር ኢትዮጵያ