ሎዛ አበራ ዛሬም ግቦች አስቆጥራለች

ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ ሎዛ አበራ ግብ ማስቆጠሯን ቀጥላለች። ምሽት በተካሄደ ጨዋታም ሁለት ጎሎች አስቆጥራለች።

ከቀናት በፊት ከምጋር ጋር በተደረገው የሱፐር ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ሐት-ትሪክ ሰርታ ቡድኗ የዋንጫ ባለቤት እንዲሆን ያስቻለችው ሎዛ አበራ ዛሬ ምሽት ቡድኗ ኪርኮፕን አራት ለባዶ ሲያሸንፍ በሃምሳ አራተኛው እና ሰማንያ ስድስተኛው ደቂቃ ሁለት ግቦች በማቆጠር የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን በሃያ ሶስት ግቦች መምራትዋ ቀጥላለች።

በመጀመርያው ዙር ላይ ከኪርኮፕ ጋር በተደረገው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረችው አጥቂዋ ዛሬ አመሻሹ በተደረገ ጨዋታም በተመሳሳይ ቡድኑ ላይ ሁለት ግቦች ስታስቆጥር በማልታ ቆይታዋ በዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሃያ ሦስት ግቦች አስቆጥራለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ