ሳላዲን ሰዒድ ይቅርታ ጠየቀ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሰበታ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ከደቂቃዎች በፊት መጠናቀቁ ይታወቃል። 

ክለቡ አሰልጣኞቹን ከሥራ በማገዱ ምክንያት በዛሬው ጨዋታ ቡድኑን በዋናነት እንዲመራ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በመሆን ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎበት ወደ ሜዳ የገባው አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ከዕለቱ ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ጋር በፈጠረው ሰጣ ገባ በ62ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካር ከሜዳ ወጥቷል።

ይህን ተከትሎ ሳላዲን ሰዒድ ለሶከር ኢትዮጵያ ብቻ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል። “ጨዋታው ካለው ጫና እና ክብደት አንፃር ነገሮችን መመልከት አለብህ በማለት በተደረገ የቃላት ልውጥ በተፈጠረ አለመግባባት ቀይ ካርድ በማየቴ በጣም አዝኛለው። የቅዱስ ጊዮርጊስን ደጋፊዎች በሙሉ ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” ብሏል።

©ሶከር ኢትዮጵያ