ወላይታ ድቻ ከአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ጋር ተለያየ

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ዳንኤል ዳዊት ከወላይታ ድቻ ጋር ተለያይቷል፡፡

ዓምና በከፍተኛ ሊጉ በነቀምቴ ከተማ ድንቅ ጊዜ ማሳለፉን ተከትሎ በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ አማካኝነት በዓመቱ ጅማሮ ለወላይታ ድቻ ፈርሞ የነበረው ፈጣኑ አጥቂ ዳንኤል ዳዊት በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንታት ላይ የመጫወት እድል ቢያገኝም አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ሳይችል ቀርቶ በመጨረሻም ከክለቡ ጋር የወራት ኮንትራት እየቀረው ተለያይቷል፡፡

ወላይታ ድቻዎች እስከ አሁን ዳንኤል ጨምሮ ከአምስት ተጫዋቾች ጋር የተለያየ ሲሆን በምትኩ ደግሞ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ