ሀዋሳ ከተማ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ የወንድ እና የሴቶች ቡድኑ በጋራ በመሆን ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል የገንዘብ ድጋፍን አድርጓል፡፡

ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገበት የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስን በተጠናከረ መልኩ ለማስወገድ በስፖርቱ ውስጥ ያሉ ተቋማት እና ግለሰቦች ድጋፎችን ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን አሁን ደግሞ የሀዋሳ ከተማ የወንዶች እና የሴቶች ቡድን አባላት ማለትም የአሰልጣኝ ቡድን አባላት፣ ተጫዋቾች እንዲሁም ደግሞ ከቢሮ ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው ላይ በመቁረጥ ከ150 ሺህ ብር በላይ ለግሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የክለቡ ደጋፊዎች በሀዋሳ ከተማ ላይ ቫይረሱን በመከላከሉ ረገድ ከፍተኛ ድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ተመልክታለች፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ