ፋሲል ከነማ ሌላኛው ምስጋና የተቸረው ክለብ ሆኗል

የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ለፋሲል ከነማ ምስጋና አቅርቧል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ከሊግ ካምፓኒው ጋር በመሆን የ2012 የኢትዮጵያ የሊግ ውድድሮች እንደሰረዙ መወሰኑ ይታወሳል። ከዚህ ውሳኔ ጎን ለጎንም ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው እስከ ኮንራት መገባደጃ ድረስ ደሞዝ እንዲከፍሉ ማሳሰቡ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጨዋቾች ማህበር ክለቦች ለተጨዋቾች ደሞዝ በአግባቡ እንዲከፍሉ ጥሪ በማድረግ በጊዜው ለተጨዋቾቻቸው ደሞዝ የከፈሉትን የወንዶች እና የሴቶች ፕሪምየር እንዲሁም የከፍተኛ ሊግ ክለቦችን ማመስገኑ ይታወሳል። ትላንትናም ይህ ማህበር ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፋሲል ከነማን አመስግኖ ደብዳቤ ልኳል።

ደብዳቤው ይህንን ይመስላል

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ