ወልዋሎ ለተጫዋቾቹ ደሞዝ ከፈሏል

ቢጫ ለባሾቹ የተጫዋቾች ደሞዝ ከፍለው መጨረሳቸው ሲገለፅ ተጫዋቾቹም የሁለት ወር ደሞዛቸውን በስምምነት መተዋቸው ታውቋል።

ደሞዝ ካልከፈሉ ክለቦች ዝርዝር ውስጥ የነበሩት ወልዋሎዎች የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍ በመዘግየቱ ምክንያት ደሞዝ ሳይከፍሉ መቆየታቸው የተገለፀ ሲሆን ከዓዲግራት ከተማ አስተዳደር እና የክለቡ ባለድርሻ ከሆነው ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ ከቀናት በፊት የተጫዋቾቻቸው ደሞዝ ከፍለው አጠናቀዋል። በተያያዘም ተጫዋቾቹ የሁለት ወራት ደሞዛቸውን ለመተው ከክለቡ ጋር ከስምምነት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ