ባህር ዳር 2ኛ ተጫዋቹን ለማስፈም ተስማምቷል

ከትላንት በስቲያ መናፍ ዐወልን ወደ ክለባቸው ለማምጣት የተስማሙት የጣናው ሞገዶቹ ዛሬ ከሰዓት ደግሞ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ በንቃት እየሰሩ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች የ10 ነባር ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ 2 ዓመታት ማራዛቸው ይታወሳል። ከትላንት በስትያ ደግሞ መናፍ ዐወልን ከአዳማ ከተማ ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ በረከት ጥጋቡ ከወልቂጤ ከተማ ለሁለት ዓመታት ውሃ ሰማያዊውን ማሊያ ለመልበስ ተስማምቷል። ይህ የአማካይ መስመር ተጫዋች በአማራ ፖሊስ እና በኢኮስኮ አሳልፎ በያዝነው የውድድር ዓመት ደግሞ በደጋረገ ይግዛው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ ሰንብቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ