ሰበታ ከተማ የአማካዩን ውል አራዝሟል

አማካዩ ታደለ መንገሻ ለተጨማሪ ዓመት በሰበታ ከተማ ቆይታን ለማድረግ ተስማማ፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ደደቢት እና አርባምንጭ ከተማ ተጫዋች በድጋሚ ተመልሶ ከተጫወተበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመልቀቅ በተሰረዘው የውድድር ዓመት በአዲስ አዳጊው ሰበታ ከተማ አምርቶ ጥሩ የውድድር ዓመትን ያሳለፈ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሰበታ ለመቆየት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ