ኢትዮጵያ ቡና ግብጠባቂ ለማስፈረም ተሰማምቷል

አቤል ማሞ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፀመ።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከመከላከያ ጋር ቆይታ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቀድሞ የሙገር ሲሚንቶ ግብ ጠባቂ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ለመጫወት ነው ቅድመ ስምምነት የፈፀመው። የቡናማዎቹ የክረምቱ የመጀመርያ ፈራሚም ሆኗል።

ከበረከት አማረ ጋር መለያየታቸው ጋር ተከትሎ ግብ ጠባቂ ፍለጋ ወደ ገበያ እንደሚወጡ ሲጠበቁ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች የግብጠባቂ ክፍተታቸው በመሙላታቸው አሁን ደግሞ በለቀቁባቸው ሌሎች ቦታዎች ተጫዎች ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ