ኢትዮጵያ ቡናዎች ሁለተኛ ተጫዋቻቸውን ለማስፈረም ተስማሙ

ከደቂቃዎች በፊት ከአቤል ማሞ ጋር መስማማታቸውን ያስታወቁት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዘካርያስ ቱጂን ለማስፈረም ተስማሙ።

ባለፈው የውድድር ዓመት ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ያሳለፈው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የግራ መስመር ተከላካይ ለቡና ለመፈረም መስማማቱን ተከትሎ ባለፈው የውድድር ዓመት ተፈጥሯዊ የግራ መስመር ተከላካይ ያልነበራቸው ቡናዎች በቀጣይ የውድድር ዓመት አማራጫቸውን እንደሚያሰፉ ይጠበቃል።

ዛሬ ተጫዋቾች ማስፈረም የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ