አሜሪካ በሚገኝ አካዳሚ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ

የሳክራሜንቶ አካዳሚ የተጫዋቾች አያያዝ እና ምልመላን መሠረት በማድረግ ለፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች የኦንላይን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

12:30 በጀመረውና ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀው ስልጠና አሜሪካ የሚገኘው የሳክራሜንቶ አካዳሚ የተጫዋቾች አያያዝ እና የምልመላ ስርዓትን ነንደ ማሳያ በመውሰድ ሲሆን የሳክራሜንቶ እግር ኳስ አካዳሚ ዳይሬክተር አሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን አማካኝነት ስልጠናው ተሰጥቷል። በተለይ በሀገራችን ያለውን የምልመላ ስርዓት መሻሻል የሚገባው በመሆኑ ይህ ውይይት ለዘመናዊ የስልጠና ስርዓት አስተዋጽኦ እንዳለው በውይይት እና ስልጠናው ተጠቁሟል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ