ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል፡፡

ተዘራ አቡቴ የቀድሞው ክለቡን ለመቀላቀል የተስማማ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ሀዲያ ሆሳዕና በ2008 ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግም ሆነ በሊጉ መልካም እንቅስቃሴን በማድረጉ ተሳትፎን ሲያደርግ ይህ አጥቂ የክለቡ ወሳኝ ግብ አስቆጣሪም ነበር፡፡ ይሁንና በገጠመው ጉዳት ለተወሰነ ጊዜ ከሜዳ ከራቀ በኋላ 2009 ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ በከፍተኛ ሊግ የክለቡ ቆይታ መልካም የውድድር ዓመታትን አሳልፎ ስልጤ ወራቤን ተቀላቅሎ ቆይታን ካደረገ ከአራት አመታት በኃላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል፡፡

ሌላኛው ለመፈረም የተስማማው አጥቂው ድንቅነህ ከበደ ነው፡፡ በ2009 በሀምበሪቾ በነበረው መልካም እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ቡናን የመቀላቀል ዕድል የነበረው ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ 2010 በአሰልጣኝ አሥራት አባተው አዲስ አበባ ከተማ አምርቶ ጥሩ ዓመትን አሳልፏል፡፡ 2011 በቢሾፍቱ ከተማ እና ዘንድሮም በቡታጅራ ከተማ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት በአሰልጣኝ አሥራት ስር በሚሰለጥኑ ክለቦች ውስጥ በመጫወት ከቆየ በኃላ ሀድያ ሆሳዕናን በአንድ ዓመት ውል ለመቀላቀል ማምሻውን ተስማምቷል፡፡

🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: