ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ አጥቂ አስፈርሟል

መከላከያዎች አጥቂዋ ሥራ ይርዳውን በዛሬው ዕለት አስፈረሙ፡፡

በዝውውሩ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ የሆኑት መከላከያዎች በቅርቡ አሰልጣኝ ስለሺ ገመቹን በመቅጠር አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ባለፈው ሳምንት ማስፈረማቸው ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋቿ ሥራ ይርዳውን በሁለት ዓመት ውል የግላቸው አድርገዋል። ከኢትዮጵያ ቡና ወደ ድሬዳዋ ከተማ በማምራት ጥሩ ጊዜያት ያሳለፈችው ሥራ ከቀናት በፊት ለአዳማ ከተማ ለመጫወት ቅድመ ስምምነት ፈፅማ የነበረች ቢሆንም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ተገኝታ ለመከላከያ መፈረሟ እርግጥ ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!