ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የአጥቂዋ ማረፊያ ሀዋሳ ከተማ ሆኗል

የአጥቂ መስመር ተጫዋቿ ረድኤት አስረሳኸኝ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅላለች፡፡

ከዱራሜ አካባቢ የተገኘችውና በደደቢት የክለብ ህይወቷን የጀመረችው ረድኤት ከዚህ ቀደም ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ከ2011 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የጌዲኦ ዲላ ወሳኝ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ካሳለፈች በኃላ ውሏ መጠናቀቁን ተከትሎ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሟ ሲያያዝ ቆይቶ የሀዋሳ ከተማ አራተኛ ፈራሚ በመሆን ክለቡን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅላለች፡፡

አዲስ አሰልጣኝ የሾመው የሀዋሳ ሴቶች ቡድን እስካሁን አራት ተጫዋቶች ሲያስፈርም የበርከታ ተጫዋቶቹን ቆይታ አራዞሟል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!