ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ስድስተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት መከላከያዎች ማምሻውን የመሐል ተከላካዩዋን ቤቴልሄም በቀለን አስፈርመዋል፡፡

ከወላይታ የዞን ውድድር ከተገኘች በኃላ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት ለጌዲኦ ዲላ በመጫወት በሂደት አቅሟን መገንባት የቻለችው ወጣቷ ተከላካይ ከሁለት ክለቦች ጋር ድርድር ስታደርግ ከቆየች በኃላ በመጨረሻም በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በመገኘት ለመከላከያ ለመጫወት ፊርማዋን አኑራለች፡፡

መከላከያ እስካሁን ቤተልሄምን ጨምሮ በድምሩ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!