ከፍተኛ ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ የነበረው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አሰልጣኝ ዳዊት ታደለን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተወዳዳሪ የሆነው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን ያወጣው። ያለፉትን ቀናት በርከት ያሉ አሰልጣኞችን ሲያወዳድር ከቆየ በኃላም አሰልጣኝ ዳዊት ታደለን በአንድ አመት የውል ኮንትራት በዛሬው ዕለት ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የአዳማ ከተማ ወጣት ቡድንን በማሰልጠን የአሰልጣኝነት ህይወቱን የጀመረው አሰልጣኙ ገላን ከተማን ወደ ከፍተኛ ሊግ በማሳደግ ሲያሰለጥን ቆይቶ ወደ ሌላኛው የከፍተኛ ሊግ ቡድን አቃቂ ቃሊቲ አምርቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!