ቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ቀጠረ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ግብ ጠባቂው ዝብሸት ደሳለኝን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡

ከ1999-2000 ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተው ውብሸት ጓንቱን ከሰቀለ በኋላ በኢትዮጵያ ቡና እና የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ የተለያዩ ቡድኖች ግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝነት የሰሬ ሲሆን ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በሚመሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ2003 ጀምሮ በግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝነት ሲሰራ ከቆየው ንዲዚዬ ኤይሚ ጋር በተሰረዘው የውድድር ዓመት አጋማሽ መለያየቱ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!