ፋሲል ከነማ ከ ድሬዳዋ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከ11ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ መጀመር አስቀድሞ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦችን እነሆ።

የነበራቸውን የዕረፍት ቀን በአግባቡ ተጠቅመው እንደመጡ እና በመቶ ፐርሰንት ውጤታማነት የጅማ ቆይታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚፈልጉ የገለፁት የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ከመጨረሻው የወልቂጤ ጨዋታቸው ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ቀርበዋል።

የጤና እክል ገጥሟቸው ማስታገሻ መርፌ ተወግተው ወደ ሜዳ የመጡት አሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን ከወልቂጤው ጨዋታ አንፃር ሁለት የአሰላለፍ ለውጦች አድርገዋል። በለውጦቹም አስጨናቂ ሉቃስ እና ሄኖክ ኢሳይያስ ወደ አሰላለፍ ሲመጡ እንዳለ ከበደ እና ያሬድ ዘውድነህ አርፈዋል።

አሰልጣኙ ዛሬ ጠንካራ ቡድን እንደሚገጥማቸው ገልፀው ጥንቃቄ አዘል የጨዋታ ምርጫ እንደሚኖራቸው የጠቆሙ ሲሆን መሐል ተከላካይ ላይ ሦስት ተጫዋቾችን በጉዳት ማጣታቸው ችግር ቢፈጥርባቸውም ውጤት ይዘው ለመውጣት እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ጨዋታው በኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሀን የዋና ዳኝነት አመራር ይሰጥበታል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
8 ይሁን እንደሻው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
16 ምንያምር ጴጥሮስ
2 ዘነበ ከበደ
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
27 አስጨናቂ ሉቃስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ


© ሶከር ኢትዮጵያ