አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ወልቂጤ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

09፡00 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ የመጨረሻ ያልናቸውን መረጃዎች እንዲህ አቅርበናል።

ከስብስባቸው ውስጥ በርከት ያሉ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ለዛሬ ማግኘት ያልቻሉት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በሰበታ ከተሸነፉበት ጨዋታ ላይ የአራት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገዋል። አሰልጣኙ ጉዳቶች ተፅዕኖ ቢኖራቸውም በፈተናዎች ውስጥ ቡድኑን ለማሻሻል እየሰሩ ስለመሆኑ ገልፀዋል። በለውጦቹም በጅማል ጣሰው ፣ ይበልጣል ሽባባው ፣ ሀብታሙ ሸዋለም እና ፍሬው ሰለሞን ምትክ ጆርጅ ደስታ ፣ ተስፋዬ ነጋሽ ፣ ዳግም ንጉሴ እና ያሬድ ታደሰ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ መጥተዋል።

ዛሬም የመጨረሻውን ጨዋታ ባደረጉበት መንገድ ኳስን ተቆጣጥረው በመጫወት በቶሎ ወደ ግብ ለመድረስ እንዳሰቡ የገለፁት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ በአዳማ ላይ ወሳኙን ድል ባሳካላቸው ቡድን ላይ ከጉዳት የተመለሰው አስቻለው ታመነን በፍሪምፖንግ ሜንሱ በመተካት መጀመርን መርጠዋል።

ፌደራል ዳኛ ሀብታሙ መንግስቴ ይህንን ጨዋታ በዋና ዳኝነት የመምራቱን ኃላፊነት የወሰዱት አርቢትር ናቸው።

ቡድኖቹ ለዛሬ ይዘውት የሚገቡት ስብስብ ይህንን ይመስላል :-

ወልቂጤ ከተማ

22 ጆርጅ ደስታ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
15 ተስፋዬ መላኩ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
20 ያሬድ ታደሰ
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሀመድ
26 ሄኖክ አየለ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
6 ደስታ ደሙ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
16 የአብስራ ተስፋዬ
18 አቤል እንዳለ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ