አሚኑ ነስሩ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል

ከሳምንታት በፊት ከወልቂጤ ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው የሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ተጫዋች አሚኑ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል።

የቀድሞ የጅማ አባጅፋር እና መቐለ 70 እንድርታ የኋላ ደጀን የነበረው አሚኑ ነስሩ በያዝነው የውድድር ዓመት ወደ ሠራተኞቹ አምርቶ ለመጫወት ፊርማው አኖሮ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖን ግን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተጫዋቹ እና ክለቡ ተስማምተው ተጫዋቹ ራሱን ነፃ አድርጎ ነበር። አሁን ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ ከሆነ ደግሞ ተጫዋቹ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል።

በተከታታይ ሁለት ዓመታት (2010 እና 2011) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ዋንጫ ከጅማ እና መቐለ ጋር ያነሳው አሚኑ በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በርካታ ግቦችን (26) ካስተናገዱ ክለቦች መካከል ቀዳሚው የሆነውን አዳማን የመከላከል አቅም ያሳድጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ